በል/ክ/ከ/ጤ/ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ የተገልጋይ መብት እና ግዴታ
የተገልጋይ መብት፡-
- በጤና ጣቢያ የሚሰጡ የጤና አገልግሎት የማግኘት፤
- ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት የማግኘት፤
- ጥራቱን የማሻሻልና የመታከም፤
- ሚስጥር የመጠበቅ፤
- ክብሩን እና ሞራሉን የመጠበቅ፤
- ያለፈቃድ ምርመራ አለማድረግ፤
- በህክምና ወቅት ለሚጋጥሙ አደጋ የህክምና አማራጭ የማወቅ መብት፤
- የጤና መረጃ የማግኘት መብት፤
- በሚሰጠው አገልግሎት ቅሬታ የማቅረብ፤
- የምርመራ ውጤት የማግኘት፤
- በሰዓቱ ሀክምና የማግኘት፤
- ስለበሽታው ጠይቆ መረዳትና ማውቅ፤
- ሲታከም የዋለበትን የህክምና ማስረጃ የመጠየቅ፤
- ህክምና የማቋረጥ፤
- የጤና ጣቢያው አቅም በላይ ሲሆን ወደ ከፍተኛ ለመሔድ ሪፈራል የማፃፍ፤
የተገልጋይ ግዴታ
- ካርድ አንዴ ካወጡ በኃላ ካርድን በጥንቃቄ መያዝ እና ቁጥሩን ቢቻል በሞባይል መዝግቦ መያዝ፤
- የነፃ ታካሚዎች የወረዳ ሥራ አስፈፃሚ የፈረሙበት የታደሰ የመታወቂያ ደብተር ሁሌ ይዘው መምጣት፤
- የዱቤ ታካሚዎች የድርጅታችሁን ማህተም ያለበትን መታወቂያ ይዛችሁ መምጣት፤
- ♦️ ለምግብ አቅራቢዎች የጤና ምርመራ ስትመጡ 1ፎቅግራፍ ይዞ መምጣት፤
- የጤና ባለሞያውን መብት የመጠበቅ፤
- ለሐኪም ትክክለኛ መረጃ የመስጠት፤
- በቀጠሮ ቀን አክብሮ የመታከም፤
- ሐኪም ባዘዘለት መሠረት መድሐኒት መውሰድ፧
- በጤና ፕሮግራም ላይ የመሳተፍ፤
- ለሚሰጠው ህክምና አስተያየት የመስጠት፤
- ወረፋን ጠብቆ የመታከም፤
- ካርድ በማውጣት የመስተናገድ፤
- የጤና ትምህርት መውሰድ፤
- የአካባቢን ፀጥታ ከመንሳት መቆጠብ፤
- የሐኪም ምክር መቀበል!
- ለጤና ጣቢያው ደንብ ተገዥ መሆን፣
- ሪፈራል ሲስተሙን ጠብቆ ማምጣት
- የግቢውን ንፅህና የመጠበቅ፤