የአገራችን የጤና ፖሊሲ ዋንኛው የትኩረት አቅጣጫ ጤናን በማጎልበትና በሽታን በመከላከል፣ መሰረታዊ የህክምና አገልግሎት ተደራሽነት ማምጣትና ጥራት ያለው አገልግሎት ማቅረብ ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካት አስፈላጊ ከሆኑ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል የጤና ተቋማትን ማስፋፋት፤ የባለሙያዎችንና የጤናው ዘርፍ አመራርን አቅም ማሳደግ፤ ውጤታማ የሆነና ለጤናው ዘርፍ የሚመጥን የአሰራርና አደረጃጀት ስርአት መዘርጋት፤ የጤና ክብካቤ የገንዘብ ማግኛ ምንጮችን ማስፋት፤ ከመንግስትና ከሌሎች ምንጮች የተገኙ ሃብቶችን አስተዳደርና አጠቃቀም ብቃት በማዳበር መሰረታዊ የጤና ፍላጎቶች እንዲሟሉ ማድረግ ዋንኞቹ ናቸው፡፡
የተመላላሽ ህክምና አገልግሎትን በተቀናጀ መልኩ በቤተሰብ ደረጃ መተግበርና አክሞ የማዳን አገልግሎትን በተደረጀ ሁኔታ በየደረጃው በመስጠት ህብረተሰቡ የራሱን ጤና በራሱ የሚጠብቅበትና በህመም ምክንያት የሚከሰተውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ መቀነስ
• የአዋቂ ተመላላሽ ህክምና የጤንነት መረጃ አገልግሎት
• ልዩ ህክምና (ጥርስ፣ቆዳ፣ዐይን፣ፊዚዮቴራፒ፣ስነ አእምሮ)
• የህሙማን መለየት፣መዝግባ፣ካሸር አገልግሎት
• ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ህክምና ክትትል (ቲቢ፣ኤአርቲ፣አባላዘር፣ቪሲቲ፣እና የበሽታ ቅኝት አሰሳ
መልዕክትዎን ይላኩ