ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ ከተማ ጤና ጽ/ቤቱ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡት ጤና ጣቢያዎች የሽልማት እውቅና ሰጠ።

የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት የ6 ወር አፈጻጸሙን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ከገመገመ ቡኋላ በአፈጻጸማቸው የላቀ ውጤት አምጥተዋል ያላቸውን ጤና ጣቢያዎችን በሽልማት ዛሬ እውቅና ሰቷል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መስፍን በየነ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት 6 ወራት ባብዛኛው የተሻለ የጤና አገልግሎት የሰጠንበት ቢሆንም የተወሰነ ክፍተትም ታይቷል ብለዋል። ሃላፊው ሲቀጥሉም በቀጣይ ጊዜያት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን ደግሞ ከስር እስር እየተከታተሉ በመቅረፍ ህብረተሰቡን በከፍታ ማገልገል አለብን ብለዋል። ለተሳታፊዎች ከመደረኩ የ2017 የ6 ወር ከ2018 በጀት አመት 6 ወር ጋር የነበረን አፈጻጸም በንጽጽር በማቅረብ የነበሩ ውጤቶችንና የታዩ ክፍተቶችን ለማሳየት ተሞክሯል። ተያይዞም የ6 ወር ቁልፍ ተግባራት ተለይተው ዝቅ ባሉት ላይ ዝቅ ያሉበት፣ የሚስተካከሉበት፣ ማን እና እንዴትመቼ መፈታት እንዳለባቸው አቅጣጫ ተሰቶባቸዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በዘመቻ ሲሰጥ የነበረው ከ9_14 አመት የልጅ አገረዶች የማህጸን በር ካንሰር ክትባት አፈጻጸሙ 100% ነው ተባለ።

የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በአስሩ ወረዳ፣ በ40 የመንግስትና የግል ት/ቤቶች ላይ እንዲሁም ከት/ቤት ውጪ ለሚገኙ ከ8ቱ ጤና ጣቢያዎች በተውጣጡ 10 የከታቢ ቡድኖች ከ9_14 አመት ለሆናቸው ሴቶች የክትባቱን ዘመቻ ያካሔደ ሲሆን ዘመቻውም ለ5 ቀናት ተሰቷል። የማህጸን በር ካንሰር የዘመቻ ክትባት ለመከተብ በክፍለ ከተማው እንደ እቅድ የተያዙት 2663 ሴቶች ቢሆኑም 2265ዎቹ ሲከተቡ አፈጻጸሙም ከ100% በላይ ነው ተብሏል። በዘመቻው ላይ እስካሁን የተሳተፉ፣ ያስተባበሩ እና አመራር የሰጡ ሁሉ የጤና ጣቢያ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎ፣ የትምህርት ጽ/ቤት አመራሮች እና የጤና ቢሮ ደጋፊዎች የሚዲያ አካላት እና የሐይማኖት ተቋማት በጽ/ቤቱ ተመስግነዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በጤናው ዘርፍ ያለውን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የእንጠያየቅ መድረክ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ

በልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ባዘጋጀው የእንጠያየቅ መድረክ ላይ በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከተገለልጋይና ከአገልግሎት ሰጪ ተወካዮች ጋር የፊት ለፊት ውይይት አካሄደ። በመድረኩም በበሽታ መከላከል፣ በጤና መድህን ሽፋን፣ በቤት ለቤት አገልግሎት ቅድመ መከላከል፣ በእናቶችና ህፃናት ጤና እንዲሁም በአጠቃላይ የጤና ሽፋን ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ መስፍን በየነ እንዳሉት መድረኩ ተገልጋዩ ማህበረሰብ በተለያዩ ጊዜያት በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንዲያገኝ እድል የሚሰጥ ከመሆኑ ባሻገር በአገልግሎት ሰጪ ተቋማትና በህብረተሰቡ መካከል መተማመንን በመፍጠር በጋራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ገልጸዋል። በዕለቱም የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የጤና ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ አድርገዋል።

image
image
image
image