የጤና ጣቢያዉ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልእክት
እንኳን ወደ ጤና ጣቢያችን በደህና መጡ። የጤና ትቋማችን ዋና ተልዕኮ ማዕከል ያደረገው “ወደ ጤና ጣቢያችን የሚመጣ እያንዳንዱ ተገልጋይ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አክብሮት የተመላበት እና ከፍተኛ ጥራት ያለው እንክብካቤ ይገባዋል” የሚል ጽኑ የቃልኪዳን መሰረት ላይ ነው። በኢትዮጵያ የጤና ጣቢያ ሪፎርም እና በሃገር ዓቀፍ የጤና ተቋማት የአገልግሎት ደረጃዎች መስፈርቶችን አሟልተን አገልግሎት የምንሰጥ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ተቋም እንደመሆናችን፣ ለማህበረሰባችን ተደራሽ፣ ውጤታማ እና በፍላጎታቸው ላይ የተመሠረተ አገልግሎት ለመስጠት ሳናሳልስ እንተጋለን።
ራዕያችን ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት ጥራት፣ የታካሚ ደህንነት፣ ተጠያቂነት እና ርኅራኄ የተላበሰ የጤና ማዕከል መገንባት ነው። አገልግሎቶቻችንን በማስረጃ ላይ ተመስርቶ በሚሰጥ እንክብካቤ (evidence-based care)፣ ተከታታይነት ባለው የሙያተኞች የሙያ ማጎልበቻ ፕሮግራም (ሲፒዲ)፣ የተሻሻለ የላቦራቶሪ እና የምርመራ አገልግሎቶች እና እንደ ኤሌክትሮኒክ የሕክምና መዝገቦች (ኢ.ኤም.አር) እና ሌሎች ዘመኑን የዋጁ የጤና ቴክኖሎጂዎችን በማጣመር እያጠናከርን እንገኛለን። በተጨማሪም ተገልጋዮች ባጠረ የጥበቃ ጊዜ አገልግሎት የሚያገኙበት፣ የተሻለ የእንክብካቤ ቅንጅት ያለበት እና የሚስብ የስራ አካባቢን እንዲያገኙ የሚረዱ የአሰራር ስርዓቶቻችንን በተከታታይነት እየገመገምን... ተጨማሪ ያንብቡ
ዶ/ር ለምለም ሞላ , በልደታ ክ/ከተማ የጄነራል ጃጋማ ኬሎ መታሰቢያ ጤና ጣቢያ ዋና ሥራ አስኪያጅ